loading
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን የኢትዮጵያ አየር ክልል ደህንነት አደጋ ላይ ነው መባሉን ‘መሰረተ ቢስ’ ሲል አጣጣለ

አርትስ 27/12/2010

የኬንያ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ማህበር የኢትዮጵያ አየር ክልል ደህንነትን በተመለከተ ያወጣው መግለጫ በፍጹም እውነት አእንዳልሆነ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ የአየር ተቆጣጣሪ ሰራተኞች የስራ አድማ በመምታታቸው በኢትዮጵያ አየር ክልል ውስጥ ምንም ዓይነት የደህንነት ስጋት ባለመፈጠሩ ማህበሩ ያወጣው መግለጫ መሰረተ ቢስ በመሆኑ ባለስልጣኑ በምንም መልኩ እንደማይቀበለው ገልጿል፡፡

ሰራተኞቹ አድማ ቢመቱም አሁንም በበቂ ሁኔታ ስልጠና በወሰዱ፤ በሙያው ዘርፍ ከፍተኛ እውቀት ባከበቱ እና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቁ ሰራተኞች ስራቸውን እያከናወኑ በመሆኑ ምንም ዓይነት ስጋት አይፈጥርም ብሏል፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የኢትዮጵያ አየር ክልል የተጠበቀ መሆኑን ለአየር መንገዶች፤ ለሃገራት አቪዬሽ ባለስልጣናት፤ ለዓለም አቀፍና ቀጠናዊ አካላትም እንደሚያረጋግጥ ገልጿል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *