የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሮና ወረርሽኝ እየተባባሰ በመምጣቱ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሮና ወረርሽኝ እየተባባሰ በመምጣቱ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ፡፡
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 30 ፣ 2012 መንግሥት የኮሮና ወረርሽኝን በተመለከተ የሚከተለው ስትራቴጂ በመከላከል ላይ ያተኮረ መሆኑንም ገልጿል፡፡ኅብረተሰቡን አስተባብሮ በባለሞያዎች ምክር መሠረት ለመከላከል መቻል፤ከመከላከል ያለፈ ነገር ሲመጣ ለማከም የሚያስችሉ ዐቅሞችን ማዳበር፤ የከፋው ነገር ከመጣም አስቀድሞ በመዘጋጀት እንደየ አስፈላጊነቱ ተገቢ ውሳኔዎችን እያሳለፉ መሄድ የወረርሽኙ መከላከያ ስትራረቴጅያዊ አካል ነዉ ብለዋል ጠቅላይሚኒስትሩ በመግለጫዉ፡፡
እስካሁንም በዚህ መንገድ ነው የተጓዝነው ያለዉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ ፡አሁን ያሉን መረጃዎች እንደሚያሳዩት በቫይረሱ የተያዙ ወገኖች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ነው ብሏል፡፡
ይሄም በመሆኑ ሁላችንም ያለንን ዐቅም ሁሉ አስተባብረን ወገኖቻችንን ከዚህ ወረርሽኝ ለመከላከልና የታመሙትንም ለማዳን ማዋል እንዳለብን ገልጿል፡ያለንበት ጊዜ ሕዝብና ሀገርን ለማዳን ሲባል አስቸጋሪ የተባሉ ውሳኔዎችን መወሰን ያለብን ጊዜ ነው፡፡ ይህም ውሳኔ፣ እንደ ግለሰብ፣ እንደ ማኅበረሰብ፣ እንደ ተቋምና እንደ መንግሥት የሚወሰኑ በመሆናቸዉ የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሮና ወረርሽኝ እየተባባሰ በመምጣጡ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ ዐውጇል ብሏል መግለጫዉ፡፡ይህም በሕገ መንግሥቱ ዐንቀጽ 93 መሠረት የተፈጸመ ነው የተባለ ሲሆን ይሄንን መሳይ ዐዋጅ ብዙ ሀገሮች ካወጁ መሰንበታቸዉም ተገልጿል፡፡ እኛ እስክንዘጋጅና ሁኔታው የግድ እስኪለን ጠብቀናል አሁን ግን ግዜዉ ሆንዋል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፡፡ሀገርን ለማዳንና ትውልድን ለመታደግ ከዚህ በላይ ልንወስን እንደምችልም መታወቅ አለበት ያለዉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ ፡ ዜጎቻችንም ከዚህ በላይ ግዴታቸውን ለመወጣት ወገባቸውን አጥብቀው መጠበቅ አለባቸው ብለዋል፡፡ከዚህ በተቃራኒ ችግሩን ለማባባስ የሚሠሩ ካሉ ግን፣ በሕጉ መሠረት የማያዳግም ርምጃ እንደሚወስዱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያውያን የሚያምርብን መረዳዳቱና መደጋጋፉ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ድኾችን እንርዳ፡ በአካባቢያችን ላሉት ዐቅመ ደካሞች እንድረስላቸው፡የቤት ተከራዮቻችንን ዕዳ እንካፈላቸው የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡የግል ባለሀብቶች የሠራተኞቻቸው ሕይወት እንዲያስጨንቃቸው አደራ እላለሁ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፡ መንግሥት የኢኮኖሚ ችግሮቻችንን ለመፍታት አስፈላጊውን ሁሉ እየወሰነ አብሯችሁ እንደሚሆን በዚህ አጋጣሚ እገልጥላችኋለሁ ብለዋል፡፡