የኢሮፓ ሊግ የጥሎ ማለፍ ተፋላሚ ቡድኖች ተለይተው ታውቀዋል
የኢሮፓ ሊግ የጥሎ ማለፍ ተፋላሚ ቡድኖች ተለይተው ታውቀዋል
አርትስ ስፖርት 05/04/2011
የ2018/19 የኢሮፓ ሊግ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች በተለያዩ ከተሞች ተካሂደዋል፡፡
አርሰናል በሜዳው ኢምሬትስ የአዘርባጃኑን ካራባግ በአሌክሳንደር ላካዜት ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 በመርታት ምድቡን በቀዳሚነት አጠናቋል፤ ከምድቡ ስፖርቲንግ ሊዝበን ቮርስክላ ፖልታቫን 3 ለ 0 በማሸነፍ በጥሎ ማለፉ አርሰናልን ተከትሎታል፡፡
ወደ ሀንጋሪ ያቀናው ቼልሲ ከሞል ቪዲ ጋር ሁለት አቻ ተለያይቷል፤ ለቪዲ አምፓዱ በራሱ ግብ ላይ እና ኔጎ አስቆጥረው ክለቡን መሪ ቢያደርጉም ዊልያን እና ጅሩ ደግሞ የሰማያዊዎቹን የአቻነት ግቦች ከመረብ አገናኝተዋል፡፡
የምሽቱ አስገራሚ ውጤት ኤሲ ሚላን በኦለምፒያኮስ የ3 ለ 1 ሽንፈት አስተናግዶ ከኢሮፓ ሊግ ውድድር ተሰናብቷል፤ የጅናሮ ጋቱሶ ስራም አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል ተብሏል፡፡
የስቴቨን ጀራርዱ ግላሰኮ ሬንጀርስ በራፒድ ቬና 1 ለ 0 ተረትቶ ከውድድር ውጭ ሁኗል፡፡
በምሽቱ ከተደረጉ ጨዋታዎች መካከል ቪያሪያል ስፓርታክ ሞስኮውን 2 ለ 0፣ አይንትራክ ፍራንክፉርት ላትሲዮን 2 ለ 1፣ ሲቪያ ክራስኖዳር 3 ለ 0፣ ቦርዶ ኮፐንሀገንን 1 ለ 0 አሽንፈዋል፡፡
ከየምድቡ እስካሁን ወደ ተከታዩ ዙር ጥሎ ማለፍ ያለፉ ቡድኖች ቼልሲ፣ አርሰናል፣ ዜኒት ፒተርስበርግ፤ ስላቪያ ፕራህ፣ ሪያል ቤቲስ፣ ሴልቲክ፣ ባየር ሊቨርኩሰን፣ ኦለምፒያኮስ፣ ቪያሪያል፣ ራፒድ ቬና፣ ሄንክ፣ ማልሞ፣ ሲቪያ፣ ክራስኖዳር፣ ዙሪክ፣ ሬድ ቡል ሳልዝበርግ፣ ዲናሞ ዛግሪብ፣ ዲይናሞ ኬቭ፣ ሬን፣ ባቴ ቦሪሶቭ፣ አይንትራክት ፍራንክፉርት፣ ፌነርባቼ፣ ስፖርቲንግ ሊዝበን፣ እና ላትሲዮ ናቸው፡፡
፣ክለብ ብሩዥ፣ ኢንተር ሚላን፣ ናፖሊ፣ ጋላታሳራይ፣ ቤኔፊካ፣ ሻክታር ዶኔስክ፣ ቪክቶሪያ ፕለዘንና ቫሌንሲያ የኢሮፓ ሊግ ተሳታፊነታቸውን አረጋግጠዋል፡፡