የኢራን ምክር ቤት ዛሪፍ መልቀቂያ እንዳይሰጣቸው ጠየቀ፡፡
የኢራን ምክር ቤት ዛሪፍ መልቀቂያ እንዳይሰጣቸው ጠየቀ፡፡
የኢራኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሀመድ ጃቫድ ዛሪፍ በድንገት መልቀቂያ ማስገባታቸው ለበርካታ ኢራናዊያን ድንጋጤን ፈጥሯል እየተባለ ነው፡፡
ዛሪፍ በቱይተር ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ እስከዛሬ በእኔ የአመራር ዘመን ለተፈጠሩ ስህተቶች ሁሉ መላው ኢራናዊያንን ይቅርታ እጠይቃለሁ ብለዋል፡፡
በሀገሪቱ ህግ መሰረት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥያቄ ፕሬዝዳንት ሀሰን ረሁኒ ካልተቀበሉት ተፈፃሚ አይሆንም፡፡
ታዲያ ይህን ተከትሎ አብዛኞቹ የኢራን ፓርላማ አባላት ሩሀኒ የዛሪፍን የመልቀቂያ ደብዳቤ ተቀብለው እንዳያፀድቁት የሚጠይቅ ፊርማ አሰባስበዋል፡፡
ፕሬስ ቴሌቭዥን እንደዘገበው 160 የሚሆኑ የፓርላማ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስራቸው እንዲቀጥሉ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል፡፡
ዛሪፍ አሜሪካን እና አጋሮቿን ፊት ለፊት በመጋፈጥ እና የሀገራቸውን ጥቅም ለማስከበር ግንባራቸውን ይሰጣሉ ሲሉ በርካቶች ይመሰክሩላቸዋል፡፡