የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ነው
የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ነው
ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በአገራዊ ሰላም እና ጸጥታ እንዲሁም የህግ የበላይነት የማስከበር ስራዎች ያሉበትን ደረጃ እየገመገመ መሆኑን የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች አዴፓ፣ ህውሃት፣ ኦዲፒ እና ደኢህዴን መነገራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
አባል ድርጅቶቹ እንዳሉት ስራ አስፈጻሚው ሀገራዊ ለውጡ ያለበት ሁኔታ በጥልቀት በመፈተሽ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ እየሰራ ነው፡፡
የኢህአዴግ የፖለቲካ ስራዎች ያሉበት ደረጃም እየተገመገመ መሆኑ ተነግሯል፡፡
በድርጅቶቹ መካከል የአመለካከትና የተግባር አንድነት እንዲኖር በሚያስችል ደረጃ፤ ነጻና ግልጽ ውይይት እያካሄዱ መሆኑን አባል ድርጅቶቹ ገልጸዋል፡፡
ስራ አስፈጻሚውም ለውጡን መምራት በሚያስችል ደረጃ እየተወያየ መሆኑንና በቀጣይ ዝርዝር መግለጫ እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡
በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በመገምገም ግንባሩን የሚያጠናክሩ ሀሳቦች፤ ሁሉንም ክልላዊ እና ሀገራዊ ሁኔታዎች ባገናዘበ መልኩ እየገመገመ መሆኑም ተገልጿል፡፡