የአፋሩ ሱልጣን ሐንፍሬ ዓሊ ሚራህ ሰመራ ገቡ::
አርትስ 30/12/2010
ወደ አፋሯ ርእሰ ከተማሰመራ ያቀኑት ሱልጣን ሐንፍሬ ከማህበረሰባቸውና ከክልሉ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በቅርቡ ከስደት ወደ አገር ቤት የተመለሱት ሱልጣኑ ሰመራ ሲገቡም ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡
ሱልጣን ሐንፍሬ አሊ ሚራህ ለስደት ከመዳረጋቸው በፊት የአፋር ክልላዊ መንግስት የሽሽግር ጊዜ ርዕሰ መስተዳደር ሆነው አገልግለዋል፡፡ ኢቢሲ እንደዘገበው፡፡