loading
የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ።

አርትስ ስፖርት 07/02/2011
ከምድብ ሀ እና ለ አንደኛ እና ሁለተኛ የሆኑ ቡድኖች ወደ ግማሽ ፍፃሜው የተቀላቀሉ ሲሆን ዛሬ እነዚህ ግጥሚያዎች ይካሄዳሉ፡፡ በዚህም ከምድብ ለ በ7 ነጥብ ቀዳሚ ሁኖ ያጠናቀቀው ባህር ዳር ከነማ በምድብ ሀ ሁለተኛ ሁኖ ከጨረሰው መከላከያ ጋር 9፡00 ላይ ይጫወታሉ፡፡ በውድድሩ የጣናው ሞገድ ቡድን ጥሩ ግስጋሴ ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህ ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላም ሌላኛው ግጥሚያ የሚከተል ሲሆን፤ በምድብ ሀ አንደኛ ሁኖ የጨረሰው የኢትዮጵያ ቡና ከምድብ ለ ሁለተኛ ሁኖ ከፈፀመው ጅማ አባ ጅፋር ጋር ይጫወታሉ፡፡ የሁለቱ ጨዋታዎች አሸናፊ የሚሆኑት ቡድኖች በተደረገው አዲስ የፕሮግራም ሽግሽግ በመጭው ቅዳሜ ለሚደረገው የዋንጫ ጨዋታ የሚያልፉ ይሆናል፤ ተሸናፊዎቹ ደግሞ በዕለቱ ከፍፃሜው ጨዋታ በፊት ለደረጃ ይጫወታሉ፡፡ በተያያዘ ዜና የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ በመጭው እሁድ ሊካሄድ የነበረ ቢሆንም የኢትዮጵያ አሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ጨዋታም በዕለቱ የሚካሄድ በመሆኑ፤ ይህን የመርሀ ግብር መገጣጠም ለማስተካከል ሁለቱም ውድድሮች ላይ ሽግሽግ ተደርጓል። የከተማ ዋንጫ ፍፃሜው ቅዳሜ ሲካሄድ የኢትዮጵያ ዋንጫ የአሸናፊዎች አሸነፊ ደግሞ ቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል፤ ጅማ አባ ጅፋር እና መከላከያ ደግሞ ተፋላሚዎች ናቸው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *