loading
የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የምድብ ሶስተኛ ጨዋታዎች ዛሬ እና ነገ ይደረጋሉ

አርትስ ስፖርት 03/02/2011

ከመስከረም 26 ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም እየተካሄደ የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ጨዋታ (ሲቲ ካፕ) ዛሬ እና ነገ በምድብ ሶስተኛ ጨዋታዎች ቀጥሎ ይደረጋሉ፡፡

በዚህም በምድብ ሀ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በሁለት የምድብ ግጥሚያዎች ሽንፈትን ካስተናገደው አዳማ ከተማ ጋር ከቀኑ 8፡00 ላይ ይጫወታሉ፡፡ 

የዚህ ጨዋታ መጠናቀቅን ተከትሎ ደግሞ ሁለት ተከታታይ ድሎችን ያስመዘገበው ኢትዮጵያ ቡና ከ መከላከያ የሚፋለሙ ይሆናል፡፡

ምድቡን ኢትዮጵያ ቡና በስድስት ነጥብ እና ስድስት ንፁህ ግቦች የሚመራ ሲሆን መከላከያ በሶስት ነጥብ ያለምንም ግብ ሲከተል ኤሌክትሪክ በተመሳሳይ ሶስት ነጥብ በአራት የግብ ዕዳ ሶስተኛ ደረጃ እንዲሁም አዳማ ከተማ ያለምንም ነጥብ በሁለት የግብ ዕዳ የምድቡ ግርጌ ላይ ተቀምጧል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና ከምድቡ ወደ ተከታዩ ዙር ለማለፍ ጫፍ የደረሰ ሲሆን መከላከያ እና ኤሌክትሪክ እኩል እድል አላቸው፤ በአንፃ ሩ አዳማ የማለፍ ዕድሉ የመነመነ ነው፡፡ 

የምድብ ለ ሶስተኛ ጨዋታዎች በነገው ዕለት የሚካሄዱ ይሆናል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *