የአዲስአበባ ከተማ የከንቲባ ፅ/ቤት ህግን ያልተከተለ ብልሹ አሰራር ሲገጥማችሁ በእነዚህ የስልክ መስመሮች ጠቁሙኝ ብሏል
የአዲስአበባ ከተማ የከንቲባ ፅ/ቤት ህግን ያልተከተለ ብልሹ አሰራር ሲገጥማችሁ በእነዚህ የስልክ መስመሮች ጠቁሙኝ ብሏል
አርትስ 07/ 04 /2011
አዲስ የተቋቋመው የጥቆማ መስጫ ማእከል ሙሉ በሙሉ በከንቲባ ፅ/ቤት ይመራል፤
ከህዝብ የሚሰበሰብ ቅሬታን እና ጥቆማን የሚያጣራ በከንቲባ ፅ/ቤት የሚመራ ግብረሃይል ተቋቁሟል፤ ከአጣሪ ግብረሃይሉ ጋር በመሆን በየዕለቱ ለከንቲባው ሪፖርት የሚያቀርብ ኮሚቴም ተቋቁሟል፤ ቅሬታ ተቀባዮቹ(ኦፕሬተሮች) ከማንኛውም አካል ነፃ እና ተጠሪነታቸውም ለከንቲባ ፅ/ቤት ብቻ የሆኑ ሲሆን ፤ ድርሻቸውም በስልክ ከህዝብ የቀረበን ጥቆማ እና አቤቱታ ለኦፕሬቲንግ ሲስተም አስተባባሪው ማድረስ ብቻ ይሆናል ብሏል ፅ/ቤቱ፡፡
የስልክ አጠቃቀሙን በተመለከተ ፤ ለእያንዳንዱ ክ/ከተማ የሚቀርብ ቅሬታ እና ጥቆማ በተሰጠው የስልክ መስመር በመጠቀም ማድረስ ይቻላል፡፡ ነገር ግን መጠቆም ያለበት በየወረዳው እና ክፍለከተማው ያለውን አመራር ብቻ ሳይሆን በህገ-ወጥ መንገድ የተያዘ የመኖሪያ ቤት ፥ የታጠረ መሬት ፥ የንግድ ሼድ እና ማንኛውንም ኢ-ፍትሃዊ ድርጊት ሲመለከት ለፅ/ቤቱ ጥቆማ በማድረግ የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ ሲል አሳስቧል፡፡