loading
የአብዴፓ 7ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ የፕሬዚዲየም አባላቱን መረጠ

የአብዴፓ 7ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ የፕሬዚዲየም አባላቱን መረጠ

አርትስ 25/03/2011

 የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /አብዴፓ/  በ7 ድርጅታዊ ጉባዔ ፤7 የፕሬዚዲየም አባላቱን የመረጠ ሲሆን አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድርሰብሳቢ ፣ኢንጂነር አይሻ መሃመድን ምክትል ሰብሳቢ አድርጎ መርጧል።

የአብዴፓ ሊቀመንበር ሃጂ ስዩም አወል በጉባዔው መክፈቻ እንደተናገሩት ስትራቴጂክ አመራር፣ የውስጥ ድርጅታዊ ዴሞክራሲ፣ የህግ የበላይነት፣ የተደራጀ ሌብነት እንዲሁም የግልና የቡድን የስልጣን ሽኩቻዎች ድርጅቱን በተለያዩ ጊዜያት የተፈታተኑት ነገሮች እንደነበሩ አንስተዋል።

በጉባዔው መክፈቻ ኢህአዴግን ጨምሮ የኦዴፓ፣ ህወሃትና ሌሎች አጋር ድርጅቶች ተወካዮች የድጋፍ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በቆይታውም 2008 . ጀምሮ በክልሉ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን በመገምገም፥ ነባር የድርጅቱን አባላትንም በክብር ይሸኛል ተብሎ ይጠበቃል።

በሚሸኙ አባላት ምትክም ሴቶችን ያሳተፈ፣ ወጣትና የተማረ ኃይልን ወደ አመራርነት በማምጣት የድርጅቱ ስራ አስፈፃሚ እና ማዕከላዊ ኮሚቴ እንዲጠናከር ይደረጋል ተብሏል።

ፋና እንደዘገበዉ በድርጅታዊ ጉባዔው 700 አባላት የታደሙ ሲሆን 594 በድምፅ የሚሳተፉ ናቸው።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *