የአሹራ በዓል በመጪው መስከረም ወር ይከበራል
አርትስ 30/12/2010
በሂጅራ ቀን አቆጣጠር በዓመቱ የመጀመሪያው ወር የሚከበረው የአሹራ በዓል፤ ˝የአሹራ በዓላችን ለሰላም ፣ ለአንድነት እና ለልማታችን˝ በሚል መሪ ቃል መስከረም 11 ቀን 2011 ከቀኑ ስድስት ሰዓት ጀምሮ በመቀሌ ከተማ ይከበራል፡፡
የዝግጅቱ ዓላማ ንጉስ ነጃሺ በዘመናቸው የሰሩትን ታሪካዊ ስራዎች እና ለአለም ሙስሊም የከፈሉትን መሰዋዕትነት ለመለው የአለም ህዝብ በቱሪዝም መልኩ ለማስተዋወቅ እንደሆነ አቶ ያሲን ረጃ የኢትዮ አልነጃሺ አስጎብኚ ዋና ስራ አስኪያጅ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል፡፡
መስከረም 11 ቀን በሚከበረው በዚህ ዝግጅት ቦታው ከሃይማኖታዊ ገፅታው በተጨማሪ የታሪክ ቅርስነቱን በተመለ ከተ በምሁራን ሰፊ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ለሚደረገውም ጉዞ የሆቴል እና የመጓጓዣ አገልግሎትን ጨምሮ ወጪው 9 ሺህ ብር እንደሆነ ተነግሯል፡፡