የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ መቀመጫዉን አስመራ ካደረገዉ ከአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ (አዲኃን) ጋር ይወያያሉ፡፡
አዲኃን ባለፉት ስምንት ዓመታት መቀመጫውን ኤርትራ አድርጎ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ስርዓት በመቃወም የትጥቅ ትግል ሲያደርግ የነበረ የፖለቲካ ፓርቲ ነዉ፡፡
የአማራ መገናኛ ብዙሃን እንዳስታወቀዉ አዲኃን ከመንግስት ጋር የሚያደርገዉ ድርድር ምን ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩር አስካሁን አልታወቀም፡፡
የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ትላንት አስመራ መግባታቸዉ ይታወሳል፡፡