የአለም አቀፉ የንግድ ምልክት ማህበር የኢትዮጵያ የፈጠራ ባለሙያዎች አለማቀፋዊ የአእምሮ ንብረት ጥበቃ እንዲያገኙ እጥራለሁ አለ
የአለም አቀፉ የንግድ ምልክት ማህበር (international trade mark association) የኢትዮጵያ የፈጠራ ባለሙያዎች አለማቀፋዊ የአእምሮ ንብረት ጥበቃ እንዲያገኙ በሚደረገው ጥረት ለማገዝ ዝግጁ ነኝ አለ፡፡
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ጀማል በከር ከአለም አቀፉ የንግድ ምልክት ማህበር የመካከለኛዉ ምስራቅ አፍሪካ ተወካይ ታት ቲነን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይቱ ላይ በኢትዮጲያ የሚመረቱ የማኒፋክቸሪንግ ምርቶች መሻሻልና ብራንድ፣የአግሮ ፕሮሰሲንግ ምርቶች ወደ አለም ገበያው በሚቀላቀሉበት ሁኔታ እና የፈጠራ ስራዎች የአለም አቀፍ አዕምሮ ጥበቃ በሚያገኙበትና በአለም ደረጃ በሚተዋወቁበት ሁኔታ መክረዋል፡፡
የአለም አቀፉ የንግድ ምልክት ማህበር በፈጠራ ስራዎች እውቅና ፣ጥበቃ፣በራንድና በሌሎች የኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙርያ ከኢትዮጵያ ጋር ለመስራት ፍላጎት እንዳለው የሳይንስና ኢኖቪሽን ሚኒስቴር ገልጿôል፡፡