loading
የአለም ባንክ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚከናወነው ብርሀን ለሁሉም ፕሮግራም 375 ሚሊየን ዶላር ፈቀደ

የአለም ባንክ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚከናወነው ብርሀን ለሁሉም ፕሮግራም 375 ሚሊየን ዶላር ፈቀደ

አርትስ 25/03/2011
የውሀ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያሳየዉ፥ ባንኩ ከፈቀደው ገንዘብ 60 ሚሊየን ዶላሩን ለስራ ማስጀመሪያ ለቋል።

በ2010 ዓ.ም ይፋ የተደረገው ይህ የብርሀን ለሁሉም ወይም የብሄራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም ከሰባት እስከ ስምንት አመት ጊዜን የሚወስድ ነው ተብሏል።

ይህም በተወሰነ የጊዜ ገደብ ተጠቃሚ ያልሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል እንደሆነ ነው በሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ብዙነህ ቶልቻ የተናገሩት።

በአሁን ወቅት የሀገሪቱ የኤሌክትሪክ ሀይል የማምረት አቅም በዓመት 4 ሺህ 200 ሜጋ ዋት መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *