የኔዘርላንድ መንግስት ለ160 ኢትዮጵያዉያን የሕግ ባለሙያዎች የሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት እድል ሰጠ
የኔዘርላንድ መንግስት ለ160 ኢትዮጵያዉያን የሕግ ባለሙያዎች የሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት እድል ሰጠ
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከኔዘርላንድ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ነዉ በፌዴራል ደረጃ ለሚገኙ 160 የሕግ ባለሙያዎች የሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት እድል የተሰጠዉ
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከኔዘርላንድ ኤንባሲ ጋር በመተባበር በፍትህ ዘርፍ አቅም ግንባታ ፕሮጀክት አማካኝነት የመንግሰት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና የኔዘርላንድ ኤምባሲ አምባሳደር በተገኙበት የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት ማስጀመሪያ ፕሮግራም ይፋ ተደርጓል፡፡
የጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ አቶ ብርሃኑ ፀጋየ እንደተናገሩት እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ጠንካራ የፍትህ ተቋም በሌላቸው አገሮች ለሕግ ባለሙያዎች ከአቅም መገንባት ጋር በተያያዘ የትምህርት እድል መሰጠቱ በፍትህ ሥርዓቱ የሚታዩትን ክፍተቶችን ለመቅረፍ ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የፍትህ ሥርዓቱን ለማሻሻል ከኔዘርላንድ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ከዚህ በፊት ከ2012 እስከ 2016 በፍትህ ዘርፍ የአቅም ግንባታ ፕሮጀክት በማዘጋጀት ከፌዴራልና ክልል ለተውጣጡ ባለሙያዎች በሁለተኛ ዲግሪ መርሃ ግብር በ6 የትምህርት አይነቶች በ2 ዙር ማሰልጠን የተቻለ ሲሆን በተጨማሪም በተለያዩ ጊዜያት አጫጭርና ረዥም ስልጠናዎች እንዲሰጣቸውም ተደርጓል ብለዋል፡፡