loading
የናይጄሪያ ሳይንቲስቶች በዋጋው ርካሽና በፍጥንት ዉጤትን ለማወቅ የሚያስችል የኮቪድ 19 የምርመራ ኪት መስራታቸዉን አስታወቁ፡፡

አዲስ አበባ፣ ህዳር 08፣ 2013 የናይጄሪያ ሳይንቲስቶች በዋጋው ርካሽና በፍጥንት ዉጤትን ለማወቅ የሚያስችል የኮቪድ 19 የምርመራ ኪት መስራታቸዉን አስታወቁ፡፡ ሲኤን ኤን እንደዘገበዉ ሳይኒቲስቶቹ ሰራነው ያሉት አዲሱ የመመርመሪያ ኪት እርካሽና በቀላሉ ማገኘት ሚያስችል ነዉ ፤ዉጤቱንም ከ 40- ደቂቃ ባነሰ ግዜ ዉስጥ ያሳዉቃል፡፡

የመመርመሪያ ኪቱን ዉጤት የሚያሳዉቅ ማሽን አዲስ የተሰራ ሳይሆን ከዚህ በፊት ለኮቪድ 19 መመርመሪያ የሚዉለዉን በማጎልብት የተዘጋጀ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ናይጄሪያ በአሁኑ ወቅት ኮቪድ 19 መመርመሪያ ኪት ከቻይና የምታስገባ ሲሆን 200 መሊዮን ዜጎቸቿን በግዢ በሚገባ ኪት መመርመር አልተቻላትም ነበር፡፡ ናይጄሪያ በኮቪድ 19 ከተጎዱ የአፍሪካ ሀገራት 9ኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሲሆን ፤ከ63 ሺህ በላይ ዜጎቿ
የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸዉ ከአንድ ሺህ አንድ መቶ 60 በላይ ሰዎች ህይወታቸዉን አጥተዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *