የትራምፕ እና ኪም ድርድር ያለስምምነት ተቋጨ፡፡
የትራምፕ እና ኪም ድርድር ያለስምምነት ተቋጨ፡፡
የዓለምን ህዝብ ትኩረት ስቦ የነበረው የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ሁለተኛ ዙር ውይይት ያለውጤት ለመበተኑ ምክንያት የኪም ማእቀብ ይነሳልኝ ጥያቄ መልስ በማለማግኘቱ መሆኑን ሲ ኤን ኤን ከስፍራው ዘግቧል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ግን ሁሌም እንደምለው መቻኮል አያስፈልግም ዋናው ነገር ብዙ ጠቃሚ ሀሳቦችን ተለዋውጠናል በማለት ነገሩን ለማለዘብ ሞክረዋል፡፡
ከአሁኑ ስብሰባ ብዙ ተጠብቆ የነበረ ቢሆንም ምንም አይነት የስምምነት ፊርማ ሳይከናወን ነው የተጠናቀቀው፡፡
በዚህ ምክንያት የሁለቱ መሪዎች ድርድር ከተያዘለት ጊዜ ቀድሞ ተጠናቅቋል ነው የተባለው፡፡
ፕሬዝዳንት ትራምፕ የፊርማ ሰነዶቹ ተዘጋጅተው ነበር፤ግን ምን ዋጋ አለው አልተፈረሙም ማለታቸውን አልጀዚራ በዘገባው አስነብቧል፡፡
እንዲያም ሆኖ ኪም ከዚህ በኋላ የኒውክሌር ሙከራ አላደርግም ማለታቸውን እና እሳቸውም እንደሚያምኗቸው ትራምፕ ተናግረዋል፡፡
መንገሻ ዓለሙ