loading
የታይዋን እና የቻይና  ፍጥጫ ወደ ጦርነት እንዳያመራ አስግቷል

የታይዋን እና የቻይና  ፍጥጫ ወደ ጦርነት እንዳያመራ አስግቷል

የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ዥንፒንግ ሰሞኑን በተደጋጋሚ አንዲት ቻይና በሚለው ፖሊሲያቸው ታይዋንን ከእናት ሀገሯ የሚለያት የለም ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ይህ ሁኔታ ደግሞ ታይዋን በየትኛውም ጊዜ ከቻይና ወረራ ይፈፀምብኛል የሚል ስጋት እንዲገባት  በር ከፍቷል ነው ተባለው፡፡

ዋሽንግተን ፖስት እንደዘገበው የሰሞኑ የቻይና አዝማሚያ ያላማራት ታይዋን በአዲሱ ዓመት ለቤጂንግ መልዕክት በሚያስተላልፍ መልኩ ወታደራዊ ልምምድ ለማድረግ ዝግጅት ላይ ናት፡፡

ቻይና በቅርቡ የሀገራችንን ሉዓላዊ ግዛት አደጋ ላይ ለመጣል እንደ አዲስ ማስፈራራት መጀመሯ  በአዲስ ስልት የተነደፈ የጦር ልምምድ እንድታደርግ አስገደዷታል ብለዋል የታይዋን ወታደራዊ አዛዦች፡፡

ታይዋን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የምትከተለው ስትራቴጂ ራስን ከመከላከል አልፎ ከቻይና ሊደርስባት ለሚችለው ጥቃት አፀፋ መስጠት ወደሚያስችላት ደረጃ ከፍ ማድረግ ላይ ያተኮረ ሆኗል ተብሏል፡፡

ፕሬዝዳንት ሺ ታይዋን ከቻይና ተነጥላ በራሷ እንድትተዳደር ከሚፈልጉት ጥቂት የታይዋን ዜጎች ይልቅ የውጭ ጣልቃ ገቦች እጃቸው ረጅም ነው በማለት አሜሪካን በጎንዮሽ ወቅሳለች፡፡

ፕሬዝዳንት ሺ ታይዋንን የሀገራችን አንድ አካል የማድረግ ህጋዊም ፖለቲካዊም መብት አለን፣ ይህን ለማድረገ ሁሉንም አማራጮች እንጠቀማለን ሲሉ የታይዋኗ አቻቸው ፃይ ኢንግ ዌን ግን ቤጂንግ ሆይ በሉዓላዊነታችን አትምጭ አርፈሽ ተቀመጭ ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

 

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *