የቱኒዚያው ፕሬዚዳንት ካይስ ሰይድ የሀገሪቱን ፓርላማ በተኑ፡፡
አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 19፣ 2013 የቱኒዚያው ፕሬዚዳንት ካይስ ሰይድ የሀገሪቱን ፓርላማ በተኑ፡፡ ፕሬዚዳንቱ የቱኒዚያዉን ጠቅላይ ሚኒስትሩንም ከስልጣናቸ አባረዋል፡፡ የፕሬዚዳንቱ ተግባር መፈንቅለ መንግስት ነው ሲሉ ተቃዋሚዎች ገልጸውታል፡፡
ሮይተርስ እንደዘገበዉ ፕሬዚዳንቱ በኮቪድ-19 ሳቢያ በሀገሪቱ የተከሰተውን አመጽ ተከትሎ ነው እርምጃውን የወሰዱት ተብሏል፡፡ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ቱኒዚያዊያን የሀገሪቱ መንግስት ኮቪድ -19ን የያዘበት መንገድ አግባብ አይደለም በሚል ለተቃውሞ ወጥተዉ ነበር፡፡ በከተማዋ ቱኒዝ እና በሌሎች ከተሞችም ለተቃውሞ የወጡ ዜጎች ለገዢዉ ፓርቲ ተቃውሟቸውን የገለጹ ሲሆን፤ የሀገሪቱ ፓርላማ እንዲበተን ጠይቀዋል፡፡