የተጭበረበረ ፡ ይህ ምስል የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በወታደሮች ተይዘው አያሳይም።
ትክክለኛው ምስል የህወሃት ከፍተኛ አመራር የነበሩት አቶ ስብሃት ነጋ በቁጥጥር ስር ውለው አዲስ አበባ ሲገቡ ያሳያል።
ልጥፉ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን መለዮ በለበሱ ወታደሮች በቁጥጥር ስር የዋሉ አስመስሎ ለማቅረብ ሞክሯል።
ልጥፉ “ዛሬ የደረሰን ሰበር መረጃ ሽመልስ አብዲሳ ታሰረ” ይላል።
የጎግል የምስል ፍለጋ (Google reverse image search) ውጤት እንደሚያሳየው የልጥፉ ትክክለኛ ምስል ጥር 1፣ 2013 ዓ.ም የህወሃት ከፍተኛ አመራር የነበሩት ስብሃት ነጋን በቁጥጥር ስር ውለው አዲስ አበባ ሲገቡ ያሳያል።
ከስር እንደሚታየው ሐሰተኛው ምስል በትክክለኛው ምስል ላይ የአቶ ሽመልስ አብዲሳን የፊት ምስል ቆርጦ በአቶ ስብሃት ነጋ ፊት ላይ በመደረብ ለማጭበርበር ሞክሯል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በወቅቱ እያካሄድኩ ነው ባለው ሕግ የማስከበር ሂደት ላይ አቶ ስብሐት ነጋን ጨምሮ የ «የጥፋት ቡድን አመራሮች» ናቸው ያላቸውን የህወሓት አመራሮችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿ ነበር።
የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት (ጨፌ) መስከረም 15/2014 ዓ.ም ባካሄደው ጉባኤ አዲሱን የክልሉን መንግሥት ሲያዋቅር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ርዕሰ መስተዳደር አድርጎ ከሾመበት ጊዜ አንስቶ አቶ ሽመልስ አብዲሳን አስከአሁኑ ሰአት በተሾሙበት ቦታ ላይ እያገለገለ እንደሚገኙ አርትስ ቲቪ አረጋግጧል።
አርትስ ቲቪ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን መለዮ በለበሱ ወታደሮች በቁጥጥር ስር የዋለ አስመስሎ ለማሳየት የሞከረውን ልጥፍ ምስል ተመልክቶ የተጭበረበረ መሆኑን አረጋግጧል፡፡
. . . . .
ይህ ልጥፍ በፌስቡክ እና በተለያዩ የማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ የፔሳቼክ የእውነታ መርማሪዎች በተከታታይ የሚያደርጉት የመረጃ ማረጋገጥ እና የተሳሳተ መረጃን የማጋለጥ ተግባር አካል ነው::
እንደ ፔሳቼክ ያሉ ገለልተኛ ሶስተኛ ወገን የእውነት መርማሪ ድርጅቶች ከፌስቡክ እና የማህበራዊ ድረ ገጾች ጋር በመጣመር የሃሰት ዜናን መለየት እንዲያስችልዎ ይሰራሉ:: ይህን የምናደርገውም በየማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ የሚመለከቱት ልጥፍ/ መረጃ መነሻቸውን በማያያዝ እና ጠለቅ ያለ ዕይታ እንዲኖርዎ በማድረግ ነው::
በፌስ ቡክ ላይ የሐሰተኛ መረጃ ወይም የተጭበረበረ የመሰልዎ አጋጣሚ አለ?እንግድያውስ በእዚህ መንገድ ጥቆማ መስጠት ይችላሉ::እንዲሁም ይህን ተጨማሪ ኢንፎርሜሽን በመጠቀም አጠራጣሪ መልዕክቶችን ለመለየት የፔሳቼክ መንገዶችን ማየት ይችላሉ::
ይህ የእውነታ ምርመራ በአርትስ ቲቪ የእውነት መርማሪ ረደኤት አበራ ተጽፎ በፔሳቼክ ም/አዘጋጅ ኤደን ብርሃኔ አርትኦት የቀረበ ነው::
አንቀጹ ለህትመት እንዲበቃ ያረጋገጠው ደግሞ የፔሳቼክ ዋ/አዘጋጅ ኤኖክ ናያርኪ ነው::
ፔሳቼክ የምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የፋይናንስ መረጃ መርማሪ ተቋም ነው :: ካትሪን ጊቼሩ እና ጀስቲን አርንስቴን በተባሉ ሰዎች የተመሰረተ እንዲሁም በአህጉሪቱ ትልቁ የሲቪክ ቴክኖሎጂ እና የጋዜጠኝነት መረጃ ቋት አቅራቢ በኮድ አፍሪካ የተገነባ ነው:: እንደ ጤና : የገጠር ልማት እና የንጹህ ውሃ አቅርቦት በመሳሰሉ መስኮች ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ከመንግስት የሚጠበቁ አቅርቦቶች ላይ የተጨባጩን ዓለም እይታችንን ሊቀርጹ የሚችሉ በይፋ በሚሰራጩ የፋይናንንስ መረጃዎችን ዙርያ ህብረተሰቡ እውነተኛ መረጃን ማገናዘብ እንዲችል ለማገዝ የሚያስችል ድጋፍ ይሰጣል:: ፔሳቼክ ሚድያዎች የሚያቀርቡትን ጥንቅርም ይፈትናል:: የበለጠ መረጃ ለማግኘት pesacheck.org. ይጎብኙ::
ፔሳቼክ ኮድ ፎር አፍሪካ ከዶቼቬለ አካዳሚያ ባገኘው ድጋፍ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሚድያዎች እንዲሁም የሲቪክ ተቋማት ጋር በመተባበር ኢኖቬት አፍሪካ ፈንድ በሚለው መስመሩ የሚያቀርበው እንቅስቃሴ ነው::