የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በደቡባዊ አፍሪካ የተከሰተው አደጋ አሳስቦኛል አለ፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በደቡባዊ አፍሪካ የተከሰተው አደጋ አስግቶኛል አለ፡፡
ሞዛምቢክ፣ማላዊ እና ዚምባቡዌ ሰሞኑን በደረሰባቸው የጎርፍ አደጋ በርካታ ዜጎቻቸው አስቸኳይ ሰብዓዊ እርዳታ መጠበቅ ግድ ሆኖባቸዋል፡፡
የመንግስታቱ ድርጅት በነዚህ ሀገራት ከ2.6 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የአደጋው ተጋላጮች መሆናቸውን በሪፖርቱ ይፋ አድርጓል፡፡
በደቡባዊ አፍሪካ የተከሰተው በፈጣን አውሎ ነፋስ የሚታገዝ ከባድ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት የበርካቶችን ህይዎት ሲቀጥፍ አሁንም ገና የገቡበት የማይታወቅ ሰዎች መኖራቸውን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ተናግረዋል፡፡
በደረሰው የመሬት መንሸራተት ሳቢያ መንገዶች በመዘጋታቸው ፍለጋውን ከባድ እንዳደረገባቸውም የነብስ አድን ሰራተኞቹ ገልፀዋል፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው አካባቢያቸውን ለቀው የተፈናቀሉት ሰዎች የእለት ደራሽ እርዳታ በአፋጣኝ ካልደረሰላቸው ለከፋ ችግር ሊዳረጉ ይችላሉ፡፡
የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ የረድኤት ድርጅቶች እንዳሉት በተለይ ሞዛምቢክ በቅርብ ጊዜ ታሪኳ እንደዚህ አይነት የከፋ አደጋ ደርሶበት አያውቅም፡፡
የተገጎዱ ሰዎች የህክም እርዳታ እንዳይደረግላቸው ሆስፒታሎች በአውሎ ነፋሱ አማካይነት መፈራረሳቸው ችግሩን የከፋ እንዳደረገው አልጀዚራ ከስፍራው ዘግቧል፡፡
መንገሻ ዓለሙ