የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ በ12ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ለማዕካዊ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ባይወዳደሩ ያላቸውን 13 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ዝርዝር ለጉባኤው አቅርቧል
አርትስ 20/01/2011
ድርጅቱ በማዕከላዊ ኮሚቴነት የማይወዳደሩ ብሎ ያቀረባቸው በትምህርት፣ በአምባሳደርነት እና በክብር የተሰናበቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በሚል ነው፡፡
ለትምህርት የሚላኩ እና አሁን በትምህርት ላይ የሚገኙ:-
• አቶ ዓለምነው መኮንን
• አቶ ለገሰ ቱሉ
• አቶ ጌታቸው ጀምበር
• አቶ ኢብራሂም ሙሀመድ
• አቶ ደሳለኝ አምባው እና
• ወይዘሮ ባንቺ ይርጋ መለሰን ባይወዳደሩ ብሎ መነሻ አቅርቧል፡፡
በክብር ቢሰናቱ ያላቸው፡-
• አቶ ደመቀ መኮንን
• አቶ ከበደ ጫኔ
• አቶ መኮንን የለውምወሰን
• ወይዘሮ ፍሬህይወት አያሌው እና
• አቶ ጌታቸው አምባየን በክብር ቢሰናበቱ ብሎ አቅርቧል፡፡
በአምባሳደርነት እያገለገሉ ያሉትን፡-
• አቶ ካሳ ተክለብርሀንና
• ወይዘሮ ዘነቡ ታደሰን ከውድድሩ ውጭ ቢሆኑ ብሎ ማዕከላዊ ኮሚቴው መነሻ አቅርቧል፡፡
ማዕከላዊ ኮሚቴው ያቀረበውን ማሻሻያ ሲያስረዳ በፌዴራል ደረጃ የሚገኙ አመራሮች ካላቸው የስራ ጫና ሙሉ ጊዜያቸውን ሰጥተው በክልሉ እንዲሰሩ ታሳቢ በማድረግ እና የአመራር መተካካት አስፈላጊ በመሆኑ ብሏል፡፡ለትምህርት የተላኩት ደግሞ ፓርቲውን በረዥም ጊዜ ማጠናከር አስፈላጊ በመሆኑ ማዕከላዊ ኮሚቴው ይህንን መነሻ ይዞ ቀርቧል፡፡
ከላይ የተጠቀሱት 13 አመራሮች ለቀጣይ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባይወዳደሩ ብሎ መነሻ ያቀረበ ሲሆን ይህ መነሻ ጉባኤው ካጸደቀው በኋላ ብቻ ተግበራዊ የሚሆነው፡፡
ጉባኤው ነገ ጠዋት ከ1፡30 ጀምሮ ይቀጥላል የተባለ ሲሆን 65 አባላትን ያካተተ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ይመረጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ከተመረጡት ውስጥም 13 ለብአዴን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይመረጣሉ፡፡
አብመድ