loading
የብራዚል ታራሚዎች በመፅሃፍት የፍርድ ጊዜያቸውን እየቀነሱ ነው::

ብራዚል ታራሚዎችዋ ባነበቡት መፅሀፍት ልክ የእስር ጊዜያቸውን የሚቀንሱበትን ህግ እየተገበረች አንደሆነ ተሰምቷል ፡፡
የሀገሪቱ መጽሔቶች ጉዳዩን በስፋት እየዘገቡት ነዉ፡፡ታራሚዎች ከሳይንስ፣ ፍልስፍና እና ሌሎቸም ዘርፎች መፅሃፎችን እንዲያነቡ ይደረጋል፡፡ ሂደቱም ታራሚው ስላነበበው መፅሃፍ አጠር ያለ ፅሁፍ ያዘጋጃል፡፡ ከዚያም በተዘጋጀለት መድረክ ስለፅሁፉ ገለፃ ያደርጋል ፡፡ከገለፃው በኋላ ነው የታራሚው ለውጥ ተገምግሞ የእስር ጊዜ እንዲቀነስለት የሚወሰነው፡፡
በህጉ መሰረት አንድ ታራሚ አንድ መፅሃፍ ሲጨርስ እና በሂደቱ ሲያልፍ 4 የእስር ቀናት ይቀነስለታል፡፡ ለአንድ ሰው በዓመት እስከ 48 ቀናት ድረስ ይቀነሳል ነው የተባለው፡፡
ይህንን አስመልክቶ የተደረጉ ጥናቶች ህጉ ጥሩ ጎን ቢኖረውም 46 በመቶ የሚሆኑ የብራዚል ታራሚዎች ማንበብ እና መፃፍ የማይችሉ በመሆናቸው መጽሀፍ በማንበብ የእስር ግዜዉ የሚቀንስ ታራሚ ቁጥር ዝቅተኛ መሆኑ አይቀርም ተብሏል፡፡

አርትስ 24/12/2010

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *