የብሩንዲ የምርጫ ኮሚሽን ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች የድምፅ ቆጠራ ውጤቱን በትግዕስት እንዲጠብቁ ጥሪ አቀረበ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣2012
የብሩንዲ የምርጫ ኮሚሽን ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች የድምፅ ቆጠራ ውጤቱን በትግዕስት እንዲጠብቁጥሪ አቀረበ ብሩንዲያዊያን ባለፈው ረቡዕ የኮሮና ቫይረስ ወረረሽኝ ሳያስፈራቸው የወደፊት ፕሬዚዳንታቸውን ወደ ስልጣን ለማምጣት የሚያስችላቸውን ድምፅ ሲሰጡ ታይተዋል፡፡ የብሩንዲ ብሄራዊ ገለልተኛ የምርጫ ኮሚሽን ቆጠራው ገና ቀናትን ስለምወስድ ከወዲሁ የሚተላለፉ የአሸናፊነት መልእክቶች እንዲቆሙ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡
ይሁን እና የተቃዋሚ መሪው አጋቶን ሩዋሳ የድምጽ ቆጠራው ገና በቅጡ ሳይጠናቀቅ ድል ቀንቶናል የሚል መግለጫ መስጠታቸው ተሰምቷል፡፡ ኮሚሽኑ ቢያንስ ውጤቱ ይፋ ይሆናል ተብሎ እስከሚታሰብበት እስከመጭው ሰኞ ድረስ በትግዕስት እንዲጠባበቁ ለፓርቲ ደጋፊዎች ጥሪ አቅርቧል፡፡
ብሩንዲን ለ15 ዓመታት የመሩት ፕሬዚዳንት ፒየር ንኩሩንዚዛ ከእንግዲህ ስልጣን በቃኝ ብለው በምጫው ባይወዳደሩም በምትካቸው የፓርቲያቸውን ዋና ፀሀፊ በእጩነት አቅርበዋል፡፡ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2015 በአወዛጋቢ ውጤት ንኩሩንዚዛ ሲያሸንፉ ውጤቱን አንቀበልም ባሉ የተቃቋሚፓርቲ ደጋፊዎች እና በመንግሽጽ መካል በጸጠረ ግጭት 1 ሺህ 200 ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል፡፡