የቅርስ ጥናት እና ጥበቃ ባለስልጣን ለላሊበላ ቅርሶች 20 ሚሊዮን ብር በጀት መድቤያለሁ አለ
አርትስ 01/02/2011
የቅርስ ጥናት እና ጥበቃ ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ፋንታ በየነ ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በዓመት ለቅርስ እድሳት ከያዘው የ37 ሚሊዮን ብር በጀት ውስጥ ለላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት እድሳት እና መጠለያ ማስነሻ የሚሆን 20 ሚሊዮን ብር መመደቡን ገልፀዋል፡፡
የኢትዩጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን ጨምሮ የሌሎች ባለድርሻ አካላት የገንዘብ እገዛም እየተጠበቀ ነዉ ብለዋል፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት ቅርሶቹን እንታደግ በሚል መሪ ሃሳብ በላሊበላ ሰላማዊ ሰልፍ መካሄዱ ይታወሳል፡፡