የቀድሞው የማሊ ፕሬዚዳንት ቡበከር ኬታ ታው ሆስፒታል ገብተዋል ተባለ::
አዲስ አበባ፣ነሐሴ 28፣ 2012 የቀድሞው የማሊ ፕሬዚዳንት ቡበከር ኬታ ታው ሆስፒታል ገብተዋል ተባለ:: በመፈንቅለ መንግስት መካሄዱን ተከትሎ ለ10 ቀናት በወታደራዊ ጁንታው ቁጥጥር ስር የነበሩት ኢብራሂም ቡበከር ኬታ በተለቀቁ በጥቂት ቀናት ውስጥ ነው ሀኪም ቤት የገቡት፡፡ አሶሼትድ ፕሬስ በዘገባው እንዳስነበበው የፕሬዚዳንቱ የጤና ሁኔታ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ እስካሁን
የተብራራ መረጃ የለም፡፡
ኤን 5 የተሰኘው የሀገሪቱ ተቃዋሚ ፓርቲ ከፕሬዚዳንቱ ጋር በፖለቲካ የአስተሳሰብ ልዩነት ቢኖረንም የጤናቸው ሁኔታ ያሳስበናል የሚል መግለጫ ሰጥቷል፡፡ ፓርቲው አክሎም ኬታ በፍጥነት አገግመው ወደ ከቤተሰቦቸቸው ጋር አደንዲቀላቀሉና ጤንነታቸው እንዲስተካከል መልካሙን ሁሉ እንመኛለን ብሏል፡፡ በዋና ከተማዋ ባማኮ ውስጥ በሚገኝ የግል የህክምና ተቋም የሚገኙት ኬታ ከስትሮክ ጋር የሚመሳሰል የህመም ምልክት እንደታየባቸው ዘ አፍሪካ ሪፖርት መረጃውን ከውስጥ አቀዋቂ ምንጮች አገኘሁት ብሎ ዘግቧል፡፡ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣር ከ2013 ጀምሮ ሀገሪቱን የመሩት ቡበከር ኬታ ላይ የተካሄደውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ በርካታ ሀገራትና አለም አቀፍ ተቋማት ድርጊቱን ማውገዛቸው የሚታወስ
ነው፡፡