የሶማሌ ክልል አዲሱ ፕሬዚዳንት አህመድ አብዲ መሀመድ የቀድሞው ፕሬዚዳንት አብዲ ሞሀመድ ኦማር ስልጣን እንዳስረከቡና ሽግግሩም በሰላም እንደተጠናቀቀ ለቢቢሲ ሶማልኛ ተናግረዋል።
የክልሉ አዲሱ ፕሬዚዳንት እንደተናገሩት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ስልጣን ለመልቀቅ በመጠየቃቸው የስራ አስፈፃሚው ኮሚቴ ጥያቄያቸውን ተቀብሎ አዲሱን የክልሉ ፕሬዚዳንት እንደመረጠም ገልፀዋል።
ሰሞኑን ከብዙ ሰዎች ሞት፣ አብያተ ክርስትያናት መቃጠልና ንብረት መውደም ጋር ተያይዞም በክልሉ የመከላከያ ሰራዊት የገባ ሲሆን በክልሉ ከነበረው አለመረጋጋትና ተቃውሞዎች ጋር ተያይዞም በማዕከላዊ መንግሥት ግፊት ምክንያት አብዲ ኢሌ ከስልጣን እንደወረዱ ብዙዎች አስተያታቸውን ቢሰጡም አዲሱ ፕሬዚዳንት ሲንከባለል የነበረ ጥያቄ እንደሆነ ያስረዳሉ።
“ስልጣን ለመልቀቅ ባለፈው አራት ዓመት ጥያቄ ቢያቀርቡም በፓርቲያቸው ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም ነበርም።”