loading
የሶማሌ ክልል ምክር ቤት የ12 ዓባላቱን ያለመከሰስ መብት አነሳ

.የሶማሌ ክልል ምክር ቤት የ12 ዓባላቱን ያለመከሰስ መብት አነሳ

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት በዛሬው እለት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው ነው የምክር ቤት አባላቱን ያለመከሰስ መብት ያነሳው።

በዛሬው እለት ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው የምክር ቤት አባላትም ከዚህ ቀደም በክልሉ ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች እና የቢሮ ሀላፊዎች የነበሩ መሆናቸው እና በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ የሚገኙ መሆናቸውም ተገልጿል።

ያለመከሰስ መብታቸው ከተነሳው የምክር ቤት አባላት ውስጥም፦

  1. ወይዘሮ ሱአት መሃመድ፦ የቀድሞ የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳደር
  2. አቶ አህመድ አብዲ፦ የቀድሞ የክልሉ የፋይናንስ ቢሮ ሀላፊ እንዲሁም በክልሉ የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር ተከትሎ ጊዜያዊ ምክትል ርእሰ መስተዳድር የነበሩ
  3. ወይዘሮ ፈርሃን አብዲ፥ የቀድሞ የክልሉ የውሃ ልማት ቢሮ ሀላፊ እና የሶህዴፓ የማእከላዊ ጽህፈት ቤት ሀላፊ
  4. ወይዘሮ መጅድ መሃመድ፦ የቀድሞ የክልሉ የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ሀላፊ
  5. አቶ አብዲ መሃመድ፦ የቀድሞ የክልሉ የእንስሳትና አርብቶ አደር ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ
  6. አቶ ኸበር አብዲ፦ የቀድሞ የክልሉ የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሀላፊ እንዲሁም የሶህዴፓ የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ የነበሩት ይገኙበታል።

ከፋና እንዳገኘነዉ መረጃ ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው የምክር ቤት አባላትም ከዚህ ቀደም በሰብአዊ መብት ጥሰት፣ በክልሉ በተለይም ሀምሌ 28 2010 ዓ.ም በተከስቶ በነበረ የፀጥታ ችግር ተሳትፈዋል በሚል እና በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ናቸዉ

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *