የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ተቋማት ሰላም ተጠናክሮ እንዲቀጥል እየሰራሁ ነው አለ
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ተቋማት ሰላም ተጠናክሮ እንዲቀጥል እየሰራሁ ነው አለ
በትምህርት ተቋማት የሚታዩ የመሰረተ ልማት ክፍተቶችን በመጠቀም ችግሮች ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ እንዳያመሩ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግሯል።
በትምህርት ተቋማት ያለው አንፃራዊ ሰላምና ፀጥታ የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ወልደ ማሪያም አስታውቀዋል።
ዩኒቨርስቲዎች የታለመላቸውን አላማ ያሳኩ ዘንድ አስፈላጊ የሚባሉት መሰረተ ልማቶችን ለማሟላት መንግስት ትኩረት አድረጎ እየሰራ መሆኑንም ሚኒስትሯ ተናግረዋል።
ክፍተቶች በታዩባቸዉ ቦታዎች ሁሉ የማረም ስራዎች እየተወሰዱ ነዉ ብለዋል ሚኒስትሯ።
የመማር ማስተማር ሂደቱ በተረጋጋ ሁኔታ እንዲቀጥልና የሀገር ሰላም እና አንድነት እንዲረጋገጥ የሁላችንንም ርብርብ እንደሚጠይቅም ተናግረዋል።
በተፈጠሩ ችግሮች ተሳትፎ የነበራቸዉ አካላቶችን አጣርቶ ለፍርድ ለማቅረብም ስራዎች እንደተጀመሩ ነው ሚኒስትሯ የተናገሩት፡፡
ዶክተር ሂሩት በቡሌሆራ ዩኒቨርስቲ የተከሰቱ ችግሮችን በአግባቡ ለመፍታት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ኤፍቢሲ እንደዘገበው ተማሪዎች በነበረው ችግር ምክንያት ለአንድ ሳምንት እረፍት እንደተፈቀደላቸዉ የገለፁ ሲሆን ከጥር 1 ጀምሮ የመማር ማስተማር ስራው እንደሚጀምር ገልፀዋል፡፡
ተማሪዎችን እስካሁን ሳይጠራ የቆየው የቴፒ ግቢም ጥሪ እንዳደረገና የባከነውን የትምህርት ጊዜ ለማካካስ እንደሚሰራም ጠቁመዋል።