የሳውዲው ልዑል መሀመድ ቢን ሳልማን በማንችስተር ዩናይትድ ግዥ ላይ አስተባበሉ፡፡
የሳውዲው ልዑል መሀመድ ቢን ሳልማን በማንችስተር ዩናይትድ ግዥ ላይ አስተባበሉ፡፡
የሳውዲ አረቢያው ልዑል አልጋወራሽ መሀመድ ቢን ሳልማን፤ ከጥቅምት ወር 2018 ጀምሮ የእንግሊዙን ማንችስተር ዩናይትድ ክለብ በ3.8 ቢሊየን ፓውንድ ሂሳብ ሊጠቀልሉት ነው የሚለው ዜና በሰፊው ሲነገር ነበር፡፡
አሁን በወጣው ሪፖርት ደግሞ የልዑል አልጋወራሹ የሚዲያ ሚንስትር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለ አስተባብለዋል፡፡
ባለፈው ሳምንት የመጨረሻ ቀናት ሰሞን በወጡ ጭምጭምታዎች ደግሞ የግሌዘር ቤተሰቦች ክለቡን የመሸጥ ውጥን እንደሌላቸው ነው፡፡
ዩናይትድ በአሜሪካውያኑ የግሌዘር ዕዝ ስር የወደቀው ወይንም የተገዛው እ.አ.አ በወርሃ ግንቦት 2005 ሲሆን ያኔ የተገዛበት ዋጋ ደግሞ 790 ሚሊዬን ፓውንድ ሂሳብ ነበር፡፡
‹‹ ልዑል አልጋወራሽ መሀመድ ቢን ሳልማን ማንችስተር ዩናይትድን ሊገዙ ነው ተብሎ የወጣው ሪፖርት ሙሉ በሙሉ የሀሰት ነው›› ሲሉ ሚኒስትሩ ቱርኪ አል- ሻባናህ አስታውቀዋል፡፡
ሰውየው ጨምረው ‹‹ ማንችስተር ዩናይትድ ከሳውዲው PIF (ፐብሊክ ኢንቨስትመንት ፈንድ) ጋር ውይይት የነበረው በስፖንሰርሽፕ ጉዳች እንጂ ለመሻሻጥ አልተነጋገረም ብለዋል፡፡
ቢቢሲ