የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ደቡብ ሱዳን የጦር ወንጀል ፈጽማለች አሉ
አርትስ11/1/2011
የዓይን እማኞች እንደሚሉት ከሆነ የደቡብ ሱዳን ወታደሮች በንጹሀን ዜጎች ላይ በርካታ ጥቃቶችን ሲፈጽሙ ነው የኖሩት፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው ወታደሮችና ሚሊሺያዎች ሴቶችን አስገድዶ በመድፈርና በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል ፣ እንዲሁም ወንድ ህጻናትን እየለዩ በመግደል ወንጀሎች ተሳትፈዋል ነው የተባለው፡፡
አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው የመብት ተቆርቋሪ ተቋም ሴቶችና ልጃገረዶ በወታደሮች ታፍነው ይወሰዱ እንደነበር ማስረጃ አግኝቻለሁ ብሏል፡፡