የሮማው ሊቀጳጳስ አባ ፍራንሲስ በኢራቅ የሚያደርጉት ጉብኝት የበርካቶችን ቀልብ ስቧል::
አዲስ አበባ፣የካቲት 26፣ 2013 የሮማው ሊቀጳጳስ አባ ፍራንሲስ በኢራቅ የሚያደርጉት ጉብኝት የበርካቶችን ቀልብ ስቧል:: ፖፕ ፍራንሲስ በኢራቅ ይፋዊ ጉብኝት ሲያደርጉ የመጀመሪያቸው ሲሆን የኮሮቫይረስ ከተከሰተ ወዲህ ዓለም አቀፍ ጉ ሲያደርጉም ቀዳሚው ነው ተብሏል፡፡ የፖፑ ጉብኝት በኢራቅ ለሚገኙ ክስርስቲያኖች ልዩ ሃይማኖታዊ ትርጉም ያለው ሲሆን በጥንታዊት ባቢሎን ዘመን ጀምሮ የነበረውን የባህልና የቋንቋ እሴቶች ትስስር ያጠናክራል ነው የተባለው፡፡
ሊቀጳጳሱ ለአራት ቀናት የሚያደርጉት ጉብኝት ዋነኛ ዓለማው በኢራቅ የሚገኙ ክስቲያኖችን ለማጋጋትና በእምነት ማጠንከር እዲሁም በሀገሪቱ በሃይማኖቶች መካከል ውይይት እዲደረግ መንገዶችን ለማመቻቸት ነው ፡፡ ፖፑ በኢራት ቀናት ቆይታቸው የደህንነታተው ጉዳይ ስጋት ውስጥ እንዳይወድቅ ኢራቅ ከ10 ሺ በላይ የፀጥታ ሰዎችን ማሰማራቷን ቢቢሲ በዘገባው አስነብቧል፡፡
በባግዳድ ቆይታቸውም በሃይማኖታቸው ሳቢያ የሚሳደዱ ክርስቲያኖቸን የማፅናናት ስራ ይሰራሉ ተብሏል፡፡ ፖፕ ፍራንሲስ ለጉዞ ከመነሳታቸው በፊት በሀገሪቱ ለሚገኙ ክስቲያኖች ባስተላለፉት መልእክት ከዓመታት ጦርነትና ሽበር በኋላ ከፈጣሪ ፈውስና ይቅርታን ለመጠየቅ እየመጣሁ ነው ብለዋል፡፡ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣር በ2003 የአሜሪካ ጦር ኢራቅ ከመግባቱ በፊት በሀገሪቱ 1.6 ሚሊዮን ገደማ ክርስቲያኖች ይኖሩ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ይህ ቁጥር ከ300 ሺህ እንደማይበልጥ ነው የሚነገረው፡፡