የሞሮኮ መምህራን በቅጥር ምክንያት ተቃውሞ አስንስተዋል፡፡
የሞሮኮ መምህራን በቅጥር ምክንያት ተቃውሞ አስንስተዋል፡፡
የሞሮኮ መንግስት ካለፈው ሶስት ዓመት ጀምሮ የመንግስት ሰራተኞች በኮንትራት ብቻ ቅጥር እንዲፈፀምላቸው የሚያዝ ህግ አውጥቷል፡፡
የዚህ አይነቱ አሰራር ቀድሞ ስራ ላይ የዋለው ደግሞ በትምህርቱ ዘርፍ መሆኑ ይበልጥ መምህራኑን አስቆጥቷል፡፡
አናዶሉ የዜና ወኪል እንደዘገበው በጊዜያዊነት የሚቀጠሩት መምህራን ከመደበኛዎቹ ጋር በደሞዝ እኩል ቢሆኑም የህክምና እና የጡረታ አበል የመሳሰሉትን ጥቅማጥቅሞች አያገኙም፡፡
ይህን ተከትሎም አምስት የትምህርት ተቋማት ማህበራት በቀጣዮቹ ቀናት የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ለአባሎቻቸው ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
ዋና ከተማዋን ራባትን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ተቃውሞው ከተጀመረ ሁለት ሳምንታትን አስቆጥሯል ተብሏል፡፡
መንገሻ ዓለሙ