loading
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) እና ጀርመን የ34 ሚሊዮን ዩሮ ስምምነት ተፈራረሙ

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) እና ጀርመን የ34 ሚሊዮን ዩሮ ስምምነት ተፈራረሙ።

 

ስምምነቱ የተፈረመው በጅቡቲ እየተካሄደ ባለው 46ኛው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የሚኒስትሮች ካውንስል ስብሰባ ላይ ነው ።

ገንዘቡ ኢጋድ በስደተኞች እና በአቅም ግንባታ ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ ለሚያካሄደው ፕሮጀክት አገልግሎት ይውላል ተብሏል፡፡

የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የሚኒስትሮች ሰብሳቢ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ 46ኛውን የሚኒስትሮች ካውንስል ስብሰባ በጅቡቲ በይፋ ከፍተዋል።

በስብሰባው የአባል አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ተሳታፊ ናቸው።

ስብሳባው ለ2 ቀናት የሚቀጥል ሲሆን የኢጋድ አሰራርን ለማዘመን በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል። በስብሰበው ማጠቃለያም የተለያዩ የማሻሻያ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።መረጃው  ከውጭጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት የተገኘ ነው፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *