loading
የማዳጋስካሩ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ድምፅ ቆጠራ እየተካሄደ ነው

አርትስ/11/04/2011

10 ሚሊዮን ዜጎች በመራጭነት የተመዘገቡበት ትላንት የተካሄደውን ሁለተኛ ዙር የማዳጋስካር ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ  ተከትሎ የምርጫው ድምፅ ቆጠራ እየተካሄደ ነው፡፡

በምርጫው ሁለት የሀገሪቱ የቀድሞ ፕሬዝዳንቶች ተፋጠዋል፡፡ የ44 አመቱ አንድሪ ራጆሊና እና የ69 አመቱ ማርክራባሞናና፡፡

አንድሪ ራጆሊና እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ 2009 እስከ 2014 ሀገሪቱን በ ፕሬዝዳንትነት መርተዋል  አሁን በተደረገው በመጀመሪያው ዙር ምርጫ ደግሞ 39 በመቶ ድምፅ አግኝተው ወደ ሁለተኛው ዙር ምርጫ አልፈዋል፡፡  ፡፡

የ69 አመቱ ማርክ ራባሞናናም እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ 2002 እስከ 2009 በፕሬዝደንትነት መርተዋል፡፡ 35 በመቶ የመራጮች ድምፅ አግኝተው ነው ውጤቱ በጉጉት እየተጠበቀ ላለው ለዚሁ ምርጫ ያለፉት ፡፡

እጩዎቹ በምርጫ የተሳተፉትን በማመስገን ውጤቱን በጉጉት እየተጠባበቅን ነው ነገር ግን የምርጫ ውጤት ምንም የይሁን ምን መከበር አለበት ብለዋል፡፡

ድምፅ ከተሰጠ በኋላ የማዳጋስካሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ክርስቲያን ኔትሴይ የምርጫ ውጤት መከበር አለበት የሚለውን የእጩዎቹን ሃሳብ አድንቀው ከውጤቱ በኋላም ደጋፊዎቻቸውን እንደሚያረጋጉ እርግጠኛ ነኝ ምክንያቱም ከዚህ በኋላ ማዳጋስካር እረፍት አልባ ጉዞ አይገባትም ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *