የመድሃኒት አያያዝ እና አገልግሎት አሰጣጥ ችግር በታየባቸው መድህኒት ቸርቻሪ ድርጅቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ ነው
የመድሃኒት አያያዝ እና አገልግሎት አሰጣጥ ችግር በታየባቸው መድህኒት ቸርቻሪ ድርጅቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ ነው
በጉዳዩ ዙሪያ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቦ ከመድሃኒት ቸርቻሪ ድርጅቶች ጋር የዉይይት መድረክ ለካሄዷል፡፡
በመድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምግብ መድሃኒት ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ወረቴ እንደ ናሙና በተመረጡ የከተማችን 86 መድሃኒት ቸርቻሪ ድርጅቶች ላይ በተደረገባቸው ጥናት የመድህኒት አያያዝ፣ የአገልግሎት አሰጣጥና ምንጫቸው የማይታወቅ መድሃኒቶችን የመጠቀም ችግሮች መኖራቸውን ማረጋገጥ መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለህብረተሰቡ ጥራቱና ደህንነቱ እና ፈዋሽነቱ የተጠበቀ የመድሃኒት አገልግሎት ተደራሽ በማያደርጉ መድሀኒት ቸርቻሪ ድርጅቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑንና ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡