የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ ልዩ ስብሰባውን እያካሄደ ነው::
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28፣ 2013 ምክር ቤቱ ልዩ ስብሰባውን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ነው እያካሄደ የሚገኘው፡፡ ምክር ቤቱ በልዩ ስብሰባው የፌዴራል መንግስትን የ2014 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ ተወያይቶ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡፡
በምክር ቤቱ ስብሰባ መክፈቻ ላይ የሃገር መከላከያ ሰራዊት ላበረከተው አስተዋፅኦ የምክር ቤቱ አባላት አድናቆታቸውን በጭብጨባ ገልፀዋል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ ስብሰባ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡