loading
የሕብረት ባንክ ባለአክሲዮኖች የባንኩ ጠቅላላ ካፒታል አምስት ቢሊዮን ብር እንዲሆን ወሰኑ

አርትስ 19/02/2011

 

የ2010 ዓ.ም. የትርፍ ምጣኔውን በ42 በመቶ በማሳደግ የትርፍ ድርሻ ክፍፍል መጠኑን ወደ 34 በመቶ ከፍ እንዲል መወሰናቸውምተገልጿል፡፡

የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ታዬ ዲበኩሉ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የሕብረት ባንክን አቅም ለማጠናከር እስካሁን ያስመዘገበውን የሦስት ቢሊዮን ብርካፒታል ወደ አምስት ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ተወስኗል፡፡ ይህም የባንኩን የማበደር አቅም ለማሳደግ ያስችለዋል፡፡ ባንኩ የካፒታሉን ወደአምስት ቢሊዮን ብር ለማሳደግ መወሰኑ ካሉት የግል ባንኮች ሁለተኛው ከፍተኛ ካፒታል የያዘ ባንክ ያደርገዋል፡፡

የባንኩ አጠቃላይ የብድር ክምችት እንዲሁም ዓምና በተመሳሳይ ወቅት ተመዝግቦ ከነበረው መጠን ጋር ሲወዳደር የ24.53 በመቶ ጭማሪበማሳየት 15.07 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡

ባንኩ ለተለያዩ የንግድ ዘርፎች ያዋለውን ብድር በተመለከተ የቀረበው ማብራሪያ፣ ከአጠቃላይ ብድር ውስጥ ለወጪ ንግድ የተሰጠው በ23.75 በመቶ  ከፍተኛውን ድርሻ እንደያዘ ያሳያል፡፡ ለኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰጠው ብድር የ15.10 በመቶ፣ የአገር ውስጥ የገቢ ንግድ የ13 በመቶእንዲሁም የግንባታ ዘርፍ የ11.6 በመቶ  ድርሻ እንደነበራቸው ታውቋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *