loading
የላል ይበላ አብያተ ክርስቲያናት ጥገና ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኝ መንግስት ኃላፊነት ወስዶ እየሰራ መሆኑ  ተገለፀ፡፡

የላል ይበላ አብያተ ክርስቲያናት ጥገና ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኝ መንግስት ኃላፊነት ወስዶ እየሰራ መሆኑ  ተገለፀ፡፡

በላል ይበላ ከተማ በተከበረው የእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የተገኙት የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው በሀገራችን ያሉ ባህላዊ እና ተፈጥሯዊ ፀጋዎች የአብሮነት፣ የፍቅር እና የአንድነታችን ምንጮች እና መገለጫዎቻችን ናቸው ብለዋል።

አምሳለ እየሩሳሌም በሆነው በቅዱስ ላል ይበላ በመላው የሀገሪቱ አከባቢዎች ለመጡ እንግዶች የተደረገው የወጣቶቹ እግር አጠባ ፣ የምግብ ግብዥ እና በሰላም ገብተው እንዲወጡ የተደረጉ ስራዎች ለሌሎች አከባቢዎች ተሞክሮ እና የቱሪዝም ገቢን የሚጨምር መገለጫችን ነው ብለዋል።
የላል ይበላው የቤዛ ኩሉ ኃይማኖታዊ ስርዓት የዓለምን ቀልብ መሳቢያ ፤ ለአማኞች ደግሞ መንፈስን የሚያድስ በመሆኑ ለትውልድ እንዲተላለፍ ይሰራል ነው ያሉት ።

እንደ አማራ መገናኛ ብዙሃን ገለፃ ዶክተር ሂሩት የላል ይበላ አብያተ ክርስቲያናት ጥገና ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኝ መንግስት ኃላፊነት ወስዶ እየሰራ ነው ፤ ህዝቡ በእውቀት ፣ በክህሎትና በፀሎት እንዲያግዘን ጥሪ አቀርባለሁ ።ዶክተሯ  ከስጋት ነፃ ለመሆን የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅቶች ተግባራት በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸዉን እና  ጥገናው በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚጀምር ተናግረዋል ።

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *