loading
የሊቨርፑል ከንቲባ ጆ አንደርሰን በአልፊልድ ለሚደረጉ ጨዋታዎች ተቃውሞ የሌላቸው መሆኑን አስታውቀዋል::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1 ፣ 2012 የሊቨርፑል ከንቲባ ጆ አንደርሰን በአልፊልድ ለሚደረጉ ጨዋታዎች ተቃውሞ የሌላቸው መሆኑን አስታውቀዋል:: የሊቨርፑል ከተማ ከንቲባ ጆ አንደርሰን በአንፊልድ ለሚደረጉ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች እና ከኤቨርተን ለሚከናወነው የደርቢ ፍልሚያ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ መቀየራቸውን አስታውቀዋል ፡፡ ከንቲባ አንደርሰን በኮሮና ቫይረስ ስጋት ከአንፊልድ እና ጉዲሰን ፓርክ ውጭ የደጋፊዎችን መሰባሰብ ላይ ትልቅ ፍራቻ ነበራቸው፡፡ ፕሪሚየር ሊጉ በፈረንጆቹ ሰኔ 17 በዝግ ስታዲየም እንደሚጀመር የተረጋገጠ ሲሆን ቀያዮቹ ከኤቨርተን እና ማንቸስተር ሲቲ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታዎች ወደፊት የሚወሰን ይሆናል፡፡ አንደርሰን ከአራት ሳምንት በፊት ከነበረን አሁን በተሻለ ሁኔታ ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡
የሊቨርፑል ከተማ ምክር ቤት የመርሲ ሳይድ ደርቢ በGoodison Park ውስጥ ይካሄድ የሚለውን በዛሬው ዕለት ይወስናል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡
ከንቲባው በሚያዚያ ወር ፕሪሚየር ሊጉ ዳግም መጀመር ላይ ስጋት ያላቸው መሆኑን እና ከሜዳ ውጭ የደጋፊዎችን የመሰባሰብ ሁኔታን ይፈጥራል በማለት ሃሳባቸውን ሰጥተዋል ፡፡ አሁን ላይ ግን ከንቲባ አንደርሰን ከThe Athletic ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ከደጋፊዎች እና ከክለቦቹ ጋር
በተነጋገረነው መሰረት የበበኩላቸውን ድርሻ የሚወጡ በመሆናቸው ጨዋታዎቹን የማድረግ ዕድል ይኖራል ብለዋል፡፡በዚህም ክለቦቻችን የሜዳ ላይ ጨዋታዎቻቸውን በራሳቸው ሜዳ ቢከውኑ ተቃውሞ እንደሌላቸው አክለዋል፡፡ የመርሲሳይድ ፖሊስ በበኩሉ “ከወንጀል እና ብጥብጥ ጋር በተያያዘ” በGoodison Park ለሚደረገው ጨዋታ “ተቃውሞ የሌለው መሆኑን” እና “ፖሊሶች የሚፈለገውን ሁሉ ለማቅረብ ዝግጁ” እንደሆነ ተናግሯል ፡፡የውድድር ዓመቱ ሊጠናቀቅ የ9 ጨዋታዎች እድሜ በቀሩት ፕ/ሊግ ሊቨርፑል የደረጃ ሰንጠራዡን በ25 ነጥብ ርቀት እየመራ ሲሆን የመጀመሪያ ጨዋታውን ሰኔ 21 ከተቀናቃኙ ኤቨርተን ጋር የሚያደርግ ይሆናል፡፡ ይህ የደርቢ ፍልሚያ ሊቨርፑል ከ30 ዓመት በኋላ የሊጉን ዋንጫ አሸናፊ ሊያደርግ የሚችልበት እድል ይኖራል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *