የሊቢያ ፍርድ ቤት ወንጀለኞች ናቸዉ ባላቸዉ 45 ሰዎች ላይ የሞት ቅጣት ፍርድ ወሰነ::
የሞት ፍርዱ የተላለፈባቸው ሰዎች ታጣቂዎች ሲሆኑ በፈረንጆቹ 2011 ትሪፖሊ ውስጥ የቀድሞውን የሀገሪቱ መሪ ሙአመር ጋዳፊን በተቃወሙ ሰዎች ላይ ተኩስ ከፍተው በመግደላቸዉ ነዉ፡፡
የሞት ቅጣት ከተላለፈባቸዉ ዉስጥ የሙአመር ጋዳፊ ልጅም ይገኝበታል ተብሏል፡፡
በሊቢያ ከጋዳፊ አገዛዝ መውደቅ በኋላ በርካታ ወንጀለኞች የሞት ቅጣት ቢተላለፍባቸውም በቁጥር ደረጃ ግን የአሁኑ ትልቁ ነው፡፡
የሞት ፍርድ ከተላለፈባቸዉ ሌላ ከ54 የሚበልጡት ላይ የአምስት ዓመት የእስር ቅጣት የተጣለባቸው ሲሆን፥ 22 ያህሉ ደግሞ በክስ ሂደት ላይ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
ሊቢያ ከሰባት ዓመት በፊት በነበረው ዓመጽ ምክንያት ወደ አለመረጋጋትና ሀገራዊ ቀውስ የገባች ሲሆን ሰላሟን ለመመለስ በመታገል ላይ ትገኛለች።