loading
የህክምና መሳሪያዎችን ከባክቴሪያ ነፃ የሚያደርግ መሳሪያ በኢትዮጵያ ሊመርት ነው፡፡

የህክምና መሳሪያዎችን ከባክቴሪያ ነፃ የሚያደርግ መሳሪያ በኢትዮጵያ ሊመርት ነው፡፡

መሳሪያው ጋዝን ብቻ በመጠቀም የህክምና መሳሪያዎችን  ነጻ በማድረግ ለድጋሚ አገልግሎት ዝግጁ እንዲሆኑ የሚያደርግ ነው፡፡
አሁን ጥቅም ላይ ያሉት መሳሪያዎች በህክምና ጣቢያዎች ውስጥ ተቀምጠው ውሃና መብራትን የሚጠቀሙ ናቸው፡፡
አይ ኤም ጂ ኢንተርናሽናል ሜዲካል ግሩፕ  በኢትዮጵ የሚያመርተዉ  ተንቀሳቃሽ መሳሪያ ግን ውሃና መብራት የማይፈልግ ሲሆን በቀላሉ ከቦታ ቦታ በማንቀሳቀስ ጥቅም ላይ የሚውል ነው ተብሏል፡፡
መሳሪያውን በኢትዮጵያ ለማምረት የሚያስችለዉን ስምምነት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር  ሹመቴ ግዛው እና ከአይ ኤም ጂ ኢንተርናሽናል የህክምና ቡድን የአፍሪካ ዳይሬክተር ዶ/ር ትግስቱ  አዳሙ ስምምነቱን ተፈራርመዋል፡፡
ተን ቀሳቃሽ  መሳሪያዉ ከኪሚካል ኢንዱስትሪዎች ጋዝ በቀላሉ ማግኘት ስለሚቻል የግብዓት ችግር እንደማይኖር ተጠቁሟል፡፡
ማንኛውንም የህክምና መሳሪያዎችን ለድጋሚ ግልጋሎት ዝግጁ የሚያደርገው ይህ መሳሪያ የውሃና መብራት እጥረት ባለበት አካባቢ የሚሰጠውን ህክምና ለማገዝ ትልቅ ሚና ስለሚኖረው ወደ ምርት እንዲገባ አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገልጽዋል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *