loading
የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ብሄራዊ ፈተና የሚሰጥባቸውን ቀናት ይፋ አደረገ

ኤጀንሲው እንዳስታወቀው የ8ኛ፣ 10ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናዎች ከግንቦት 21 እስከ ሰኔ 7 ድረስ እንደሚከናወኑ ይፋ አድርጓል::

የኤጀንሲው የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ረዲ ሽፋ የፈተና መስጫ ቀናቱ ለሁሉም ክልሎች መላኩን ገልጸዋል።

ከዚህ አንጻርም ክልሎቹ የተለየ ምክንያት ካላቸው ሌላ የፈተና መስጫ ቀን በመምረጥ ለኤጀንሲው ማሳወቅ እንደሚችሉም  ተናግረዋል።

በዚህም መሰረት ብሄራዊ ፈተና የሚሰጥባቸው ቀናት ፤

የ10ኛ ክፍል ከግንቦት 21 እስከ 23 ቀን 2011 ዓ.ም

የ12ኛ ክፍል ከግንቦት 26 እስከ 30 ቀን 2011 ዓ.ም

የ8ኛ ክፍል ደግሞ ከሰኔ 5 እስከ ሰኔ 7 ቀን 2011 ዓ.ም እንደሚሰጥ ኤጀንሲው ገልጿል።

ዘገባው የኢዜአ ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *