loading
ዜጎች በምርጫ የሚሳተፉባቸው አማራጭ መንገዶች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2013 በምርጫ ወቅት ዜጎች በንቃት የሚሳተፉባቸው በርካታ አማራጭ መንገዶች መኖራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ገለጹ፡፡ በሀገራችን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲወለድ የዜጎች ንቁ ተሳትፎ እጅግ ወሳኝ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንንም በተግባር ሊያረጋግጡ ይገባል ብለዋል፡፡ ዜጎች በምርጫ ወቅት ተሳትፎአቸውን ከሚያረጋግጡባቸው መነገዶች አንዱ ካርድ ወስደው በሰላማዊ መንገድ የሚሆናቸውን ለመምረጥ ራስን ከማዘጋጀት ይጀምራል ነው ያሉት፡፡

ከዚህ በዘለለደግሞ በሲቪክ ማኅበራት አማካኝነት የምርጫው ሂደት ግልጽና ተአማኒ እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ይጠበቃልም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡ ለአብነት ያህልም በካርድ አሰጣጡ ዙሪያ፣ የምርጫ ቅስቀሳን በተመለከተ እና የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ላይ ቁጥጥር ማድረግ ሌላ መነገድ መሆኑንም ጠቅመዋል፡፡ በተጨማሪም ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን በቅድመና ድህረ ምርጫ ወቅት የሚያጋጥሙ ግጭቶችን ለማስቀረት ዜጎች የማይተካ ሚና እንዳላቸው መዘንጋት የለበትም ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገፀቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ አሳስበዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *