loading
ዛሬ ተጠባቂው የማድሪድ ደርቢ ይከናወናል

ዛሬ ተጠባቂው የማድሪድ ደርቢ ይከናወናል

 

የስፔን የ23ኛ ሳምንት መርሀግብር ዛሬ አራት ግጥሚያዎች ሲከናወኑ በማድሪድ ደርቢ አትሌቲኮ ማድሪድ በዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ ስታዲየም ሪያል ማድሪድን ያስተናግዳል፡፡ ይህ የደርቢ ፍልሚያ እ.አ.አ በ1906 ለመጀመሪያ ከተከናወነበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን በሁሉም ውድድሮች 221 ያህል ግጥሚያዎችን ተከናውነዋል፡፡ ሎስ ብላንኮስ በ109ኙ ድል ሲያደርጉ አትሌቲኮ ደግሞ በ56ቱ ላይ የበላይነታቸውን አሳይተዋል፡፡

ክለቦቹ በመጀመሪያው ዙር ሳንቲያጎ ቤርናቤው ላይ ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ማጠናቀቃቸው ይታወሳል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች በላሊጋው ለ164ኛ በአጠቃላይ ደግሞ ለ222ኛ ጊዜ፤ የደርቢ ግጥሚያቸውን ምሽት 12፡15 ላይ ያደርጋሉ፡፡ ሄታፌ ከሴልታ ቪጎ፣ ኢስፓኞል ከራዮ ቫዬካኖ እና ጂሮና ከሁሴካ ነገ የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው፤ ዕሁድ ደግሞ የሊጉ መሪ ባርሴሎና ወደ ባስክ አቅንቶ ሳን ማሜስ ላይ አትሌቲኮ ቢልባኦን ይጎበኛል፡፡

ቫሌንሲያ ከሪያል ቤቲስ፣ ሲቪያ ከኤይባር በዕለቱ ከሚከናወኑት ግጥሚያዎች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *