ወጋገን ባንክ በ2012 በጀት አመት የ46.9 በመቶ እድገት በማሳየት ከታክስ በፊት 1.1 ቢሊዮን ብር አተረፈ::
አዲስ አበባ፣ሐምሌ14፣ 2012 ወጋገን ባንክ በ2012 በጀት አመት የ46.9 በመቶ እድገት በማሳየት ከታክስ በፊት 1.1 ቢሊዮን ብር አተረፈ::ይህም ከባለፈዉ ተመሳሳይ አመት ጋር ሲነፃፀር የ46.9 በመቶ ወይም የ344.7 ሚሊዮን ብር ብልጫ እንዳለዉ ተገልጽዋል፡፡የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ አባይ መሃሪ የባንኩን የ2012 በጀት አመት የስራ አፈፃጸም ላይ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት የኮሮና ወረርሽኝ በኢኮኖሚዉ እንቅስቃሴ ላይ በፈጠረዉ መቀዛቀዝ ምክኒያ በብድር አከፋፈልና ተቀማጭ ሂሳብ አሰባሰብ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ያሳደረና ይህንንም ተከትሎ የብድር ወለድ ምጣኔ ቅናሽ የተደረገ ቢሆንም ባንኩ በ2012 በሁሉም መመዘኛዎችና የስራ ዘርፎች አመርቂ ዉጤት ማስመዝገቡን ገልፀዋል፡፡በበጀት አመቱ መጨረሻ የባንኩ አጠቃላይ የደምበኞች ተቀማጭ ሂሳብ መጠን 30.1 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን ከአለፈዉ ተመሳሳይ በጀት አመት ከነበረዉ 23.5 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነጻፅር የ27.8 በመቶ እድገት ወይም የ6.5 ቢሊዮን ብር ጭማሪ ማሳየቱን የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ አባይ ተናግረዋል፡፡በተያያዘም ባንኩ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የ1 ሚሊዮን ብር ዋና ፀሃፊዉ ዶክተር መሸሻ ሸዋረጋ በተገኙበት ድጋፍ አድርጓል፡፡ወጋገን ባንክ በበጀት አመቱ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ተጨማሪ 42 ቅርንጫፎች የከፈተ ሲሆን ባጠቃላይ የቅርንጫፎቹን ብዛትም 382 አድርሷል፡፡