ኮሚሽኑ የህዝብ ሀብት በሚዘዋወርባቸው የግል ተቋማት ላይ የሚፈፀሙ ምዝበራዎችን አጠናለሁ አለ
ኮሚሽኑ የህዝብ ሀብት በሚዘዋወርባቸው የግል ተቋማት ላይ የሚፈፀሙ ምዝበራዎችን አጠናለሁ አለ
አርትስ 20/02/2011
የ80 ሰዎችን ሃብት ለማጣራት አቅዶ ማከናወን የቻለው የ23 ሰዎችን ብቻ ነው።
የፌዴራል ስነምግባርና ጸረሙስና ኮሚሽን ከተለያዩ ተቋማት ጋር በ2010 በጀት አመት አፈፃፀምና በ2011 ዓ.ም እቅድ ላይ ውይይት ባደረገበት ወቅት እንዳስታወቀው የህዝብ ሀብት በሚዘዋወርባቸውየግል ተቋማት የሚፈፀሙ ምዝበራዎች ላይ ጥናት ሊጀምር ነው።
ተቋማቱ ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለበት የአሰራር ሥርዓት እንዲኖራቸው አደርጋለሁ ያለው ኮሚሽኑ በ2010 በጀት ዓመት ከ13 ሺህ በላይ የሀብት ምዝገባ ማድረጉን ገልጿል።
ኮሚሽኑ በሪፖርቱ ባለፈው አመት ያቀድኳቸውን አብዛኞቹን ተግባራት አሳክቻለሁ ቢልም ሃብታቸውን ከመዘገበው 13 ሺህ ሰዎች ውስጥ የ80 ሰዎችን ሃብት ለማጣራት እቅድ ይዞ ማከናዋን የቻለው የ23 ሰዎችን ብቻ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
በውይይቱ ላይ እንደተነሳው ሃሳብ እየተፈጸመ ያለው ምዝበራና ሌብነት ኢትዮጵያ የምታስገነባቸው ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ከማጓተቱም ባለፈ የግንባታ ወጪያቸውንም እያናረው ነው፡፡