ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ አዲስ አበባ ገቡ
ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ አዲስ አበባ ገቡ
አርትስ 19/02/2011
በደርግ ዘመነ መንግስት እ.ኤ.አ ከ1983-86 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩትና የወቅቱን የአገዛዝ ሰርዓት በመቃወም በፈቃዳቸው ስልጣን የለቀቁት ኮሎኔል ጎሹ ወልዴዛሬ አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን በቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሂሩት ዘመነን ጨምሮ ሌሎች የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ከኮ/ል ጎሹ ወልዴ ጋር በአሜሪካ ተገናኝተው በተወያዩበት ወቅት ኮ/ል ጎሹ ወደ አገራቸው ተመልሰው ለሚወዱት ህዝብበዕውቀትና ልምዳቸው በማገልገል የሚችሉትን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ የቀረበላቸውን ጥያቄ ተከትሎ ነው ወደሃገራቸው የተመለሱት፡፡
ኮ/ል ጎሹ እንደተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የጀመሩት የለውጥ፣ የዴሞክራሲና የነፃነት ንቅናቄ በኢትዮጵያ ታሪክ ሰፊ ህዝባዊ መሰረት ያገኘና ካመለጠተመልሶ ሊገኝ የማይችል ዕድል በመሆኑ ሁሉም አካል የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ተጠቅሞ አዎንታዊ አስተዋፅኦ ሊያበረክት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡