loading
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ማድሪድን በክለቡ ፕሬዚዳንት ምክንያት እንደለቀቀ አስታወቀ

አርትስ ስፖርት 19/02/2011

ፖርቱጋላዊው አጥቂ ሮናልዶ በሪያል ማድሪድ የዘጠኝ አመታት ቆይታው አራት የቻምፒዮንስ ሊግ እና ሁለት የላሊጋ ክብሮችን ጨምሮበአጠቃላይ 15 ታላላቅ ዋንጫዎችን ማንሳት ችሏል፡፡ ተጫዋቹ ከክለቡ ጋር ባሳለፍነው ክረምት ከተለያየ በኋላ ዩቬንቱስን ተቀላቅሏል፡፡ ያኔክለቡን ሲለቅ ለአዲስ ፈተና በራሱ ፍላጎት እንደነበር የተነገረ ቢሆንም አሁን ተጫዋቹ ከፍራንስ ፉትቦል ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ በክለቡፕሬዚዳንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ምክንያት ከክለቡ እንደተለያየ ተናግሯል፡፡ ሮናልዶ በክለቡ ውስጥ በተለይ ፕሬዚዳንቱ ያኔ ቤርናባውን የረገጠጊዜ ይመለከቱት የነበረበት መንገድ፤ ያደረጉለት የነበረውን እንክብካቤ፤ አሁን ላይ ተመሳሳይ እንዳይደለ በተለይ ባለፉት አራት አመታት ነገሮችእየተቀየሩ መምጣታቸውን ያስታወቀ ሲሆን እርሱን ለቢዝነስ ፍጆታ ብቻ አንደሚፈልጉት እንደተረዳ አስታውቆ ከዚያም ክለቡን ስለመልቀቅማሰቡን ተናግሯል፡፡ መልቀቁ ከአሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን ጋር እንደማይገናኝም አስታውቋል፡፡ የአምስት ጊዜ ባላንዶር አሸናፊው ወደዩቬንቱስም የመጣው ለገንዘብ ሳይሆን እርሱ ላይ በጣም ከልብ ፍላጎት በማሳየታቸው እንደሆነ ተናግሯል፡፡ ወደ አሮጊቷም ቤት ለገንዘብ ብሎእንዳልመጣና፤ ለገንዘብ ቢሆን ኖር ወደ ቻይና ሊያቀና እንደሚችል አስታውሷል፡፡ ሮናልዶ የዚህ አመት የባላንዶር ክብርም እንደሚገባውጨምሮ ተናግሯል፤ ዘ ጋርዲያን እንደዘገበው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *