loading
ኬንያ የዋና አየር መንገዷን ተርሚናል ለጊዜው ዘግታለች፡፡

ኬንያ የዋና አየር መንገዷን ተርሚናል ለጊዜው ዘግታለች፡፡

ናይሮቢ በሚገኘው ጆሞ ኬንያታ አየር መንገድ ተርሚናል በእቃ ማስተላለፊያው ክፍል የተነሳ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ነው ኬንያ ይህን እርምጃ እንድትወስድ ያስገደዳት፡፡

የኬንያ አየር መንገድ ባለ ስልጣናት እንደተናገሩት ተርሚናሉ አገልግሎቱን እንዲያቆም የተደረገው መንገደኞች አደጋ እንዳይደርስባቸው ከአካባቢው ለማሸሽ ነው፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው በአየር መንገዱ የእሳት ቢነሳም በመንገደኞችንም ሆነ በሰራተኞች ላይ ምንም ጉዳት አልደረሰም፡፡

የጆሞ ኬንያታ አየር መንገድ የኢትዮጰያ አየር መንገድን ጨምሮ የቱርክ፣ የእንግሊዝ እና የኤሜሬትስ አየር መንገዶችን በማስተናግድ ይታወቃል፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *